ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን የፈጸሙት ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ ወሎ ሰፈር ሸዋ ሱፐር ማርኬት አካባቢ ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ ነው። ወንጀል ፈፃሚዎቹ ኮድ 1- 09609 ትግ በሆነ ሚኒባስ ሁለቱ ሴቶች ተሳፋሪ አንደኛው ረዳት በመምሰል የግል ተበዳይ የሆነቸውን ወ/ት ሌሊሴ ያደታን ካሳፈሩ በኋላ አንደኛዋ ወንጀል ፈፃሚ ያመማት በመስመሰል የግል ተበዳይ ላይ ምራቅ በመትፋት ሌሎቹ ደግሞ የሚጠርጉ መስለው ግምቱ 40ሺ ብር የሚያወጣ የእጅ ስልኳን ከሰረቁ በኋላ ከመኪናው ላይ ገፍትረው በማስወረድ ያመልጣሉ፡፡
የግል ተበዳይ ያሰማችውን የድረሱልኝ ጥሪ የሰሙ በወንጀል መከላካል ስራ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እና በአካባቢው በነበሩ ግለሰቦች ትብብር ሦስቱ ወንጀል ፈፃሚዎች ከግል ተበዳይ ከሰረቁት ሞባይል ስልክ እንዲሁም አንድ ሌላ ተጨማሪ ስልክ እጅ ከፍንጅ እንደተያዙ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የላንቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ክትትል እንደኛዋን ወንጀል ፈፃሚ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ደጋጋሚ መሆናቸውን መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ፖሊስ አስታውቋል።
ተመሳሳይ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሠቡ ትራንስፖርት ሲጠቀም አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ ለፀጥታ አካላት ማሳወቅ እንዳለበት ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

2 Responses