ተጠርጣሪው ያሬድ ሳሙኤል ይባላል መተዳደሪያውን ጎዳና ላይ ያደረገ ሲሆን በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ ኩኩ ሰብስቤ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም በተለያዩ ቦታዎች እየተንቀሳቀሰ ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ይፈፅም እንደነበረ ለፖሊስ በሰጠው ቃል ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪ ያሬድ ሳሙኤል በአካባቢው ካልተመቸው ህመምተኛ መስሎ መንገድ ዳር በመተኛት ከወጪ ወራጁ ምፅዋት የሚጠይቅ ሲሆን መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰው እይታ ውጪ የሆነ መስሎት ከቆመ ተሸከርካሪ ላይ የ10 ሺ ብር ዋጋ ያለው ስፖኪዮ በመገንጠል ሰርቆለማምለጥ ሲሞክር በፖሊስ እጅ ላይ ወድቋል፡፡
ከክ/ከተማው ፖሊስ ባገኘነው መረጃ መሰረት ምርመራ የማስፋት ስራ መቀጠሉን ገልጿል፡፡
አንዳንድ ወንጀል ፈፃሚዎች በተለያዩ ቦታዎች ላይ በመንቀሳቀስ ካልተመቻቸው ችግረኛ እና ህመምተኛ በመምሰልና እርዳታ በመጠየቅ ምቹ ሁኔታ ካጋጠማቸው ደግሞ ልዩ ልዩ ወንጀሎችን እንደሚፈፅሙ ህብረተሰቡ ይወቀዉ ሲል የአዲስአበባ ፖሊስ አሳስቧል።

2 Responses