አሜሪካ ፥ የኬንያ መንግስት ከሰሞኑ አጋጥሞት የነበረዉን ተቃዉሞ ያበረደበትን መንገድ አድንቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በአፍሪካ ስላለው ሁኔታም በስልክ ተወያይተዋል ተብሏል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የኬንያውን ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶን ያለውን ውጥረት ለመቀነስ የወሰዱትን ርምጃ አድንቀዉ ከተቃዋሚዎች እና ከሲቪል ማህበረሰቡ ጋር ለመወያየት ቃል ስለገቡ ፕሬዝዳንት ሩቶ አመስግነዋል” ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ጠቅሷል።
ፕሬዚዳንት ሩቶ በመላ ሀገሪቱ ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞ ያስነሳና ከ 20 በላይ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን አከራካሪ የግብር ረቂቅ ህግ አንፈርምም ማለታቸዉ ይታወሳል።
የኬንያ ወጣቶች ከሰሞኑ ይህን የግብር ረቂቅ ህግን በመቃወም ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎችን እንዳደረጉና ከፖሊስና ጸጥታ አካላት ጋር ግጭት ዉስጥ ገብተዉ እንደነበር ይታወሳል። ተቃዉሞዉ በፈጠረዉ ጫናም መንግስት ረቂቅ ህጉን ዉድቅ አድርጎታል። በተቃዉሞዉ ከጸጥታ አካላት ጋር ግጭት ዉስጥ ከገቡ ሰዎች ዉስጥ ከ 20 በላይ ያህሉ ህይወታቸዉ አልፏል።
በበረከት ሞገስ

2 Responses