በቤንች ሸኮ ዞን በሼይቤንች ወረዳ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በዝሆነ በሽታ ለተጠቁት የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል ።
የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት በጽህፈት ቤቱ ስር በሚገኙ ስድስት ጤና ጣቢያዎች በዝሆነ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ በወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት የእናቶችና ህፃናት ቡድን መሪ አ/ቶ ሰለሞን ሀይለማሪያም ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።
ለተጠቃሚዎች የህክምና አገልግሎቱን ለመስጠት ከወረዳው የተውጣጡ የህክምና ባለሙያዎች ስልጠና መውሰዳቸው አንስተዋል ። በዚህም መሠረት ህክምናው በተጠናከረ ሁኔታ ተሰጥቶ ከ200 በላይ ሰዎች አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀዋል ።
በቀጣይም የሚሰጠው ህክምና የሚቀጥል መሆኑና አገልሎቱ ለተሰጣቸው የሚደረገው ክትትል ቀጣይነትም ያለው ነው ብለዋል ። የተደረጉ ድጋፎች እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን የዝሆነ በሽታ በስፋት በመኖሩ እንዲሁም በሽታው እግር ላይ የሚከሰት በመሆኑ በዚሁ በሽታ ለተጠቁ ሰዎች የሚሆን የጫማ ግባት ችግር እንዳለ ተጠቁሟል ።
አያይዘውም በሽታው በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው ያነሱት አ/ቶ ሰለሞን በተለይም ተጠቂዎች ከፈጣሪ እንደሆነም የማሰብ ሁኔታም እንዳለ ተናግረዋል ።
በአበረ ስሜነህ

2 Responses