የአሶሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነችውን ግለሰብ በጩቤ ሶስት ቦታ በጀርባዋ በመውጋት የግድያ ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱ ይታወሳል።
ሆኖም በይግባኝ በእድሜ ልክ እስራት መቅጣቱን በአሶሳ ከተማ አስተዳደር የወረዳ አንድ ፖሊስ አስታውቋል ።ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በግምቱ ከጧቱ 2፡45 ሰዓት አከባቢ ተከሳሽ አ/ቶ ዩሀንስ መርጋ ኢተቻ የተባለው ግለሰብ የሴት ጓደኛው የሆነችው ተማሪ ደራርቱ ለሜሳ የተባለችው ላይ ጭካኔ በተሞላበት የግድያ ወንጀል ፈፅሟል።
ተከሳሽ በፈፀመው ሰው መግደል ወንጀል ተከሶ ከዚህ በፊት የ18 ዓመት እስራት ውሳኔ ተላልፎበት ነበር ።ይሁን እንጅ በውሳኔው ቅር የተሰኘው የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አቃቤ ህግ ይግባኝ በመጠየቅ የእስራቱ ውሳኔ እንዲሻሻልላቸው በጠየቀው መሠረት ጉዳዩን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሲመለከተው ቆይቷል ።
ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ሲመርምር ከቆየ በኃላ የኢ/ፌ /ድ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 539 /1ሀ ስር የተመለከተው መተላለፉ ካረጋገጠ በኃላ ተከሳሹ በተከሰሰበት ወንጀል ጥፋተኛ በመሆኑ በይግባኝ ችሎት ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት እሱንም ያርማል ማህበረሰቡንም ያስተምራል በማለት በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እንድቀጣ ወስኗል ።
በአበረ ስሜነህ

2 Responses