በአሜሩካ አንድ የኒውዮርክ ከተማ ነዋሪ የሆነ ሙዚቀኛ አምስት የተለያዩ ሴቶችን በተመሳሳይ ጊዜ የልጆች አባት ሊያደርጉት መሆኑን በማስመልከት ከሁሉም ጋር በጋራ ቤቢ ሻወር የተሰኘውን ዝግጅት በማዘጋጀቱ ውዝግብ አስነስቷል።
የ22 አመቱ የኒውዮርክ ከተማ ሙዚቀኛ ዜዲ ዊል የሚባል ሲሆን የበርካቶችን ትኩረት የሳበውን አምስት ወጣት ሴቶችን ነፍሰ ጡር እንዲሆኑ ከማድረግ ባለፈ በጋራ አንድ ዝግጅት ላይ እንዲሳተፉ ማሳምኑ አነጋጋሪ አድርጎታል። ይህ አስገራሚ ይፋ ያደረገችው ከሴቶቹ መካከል አንዷ የሆነችው ሊዚ አሽሌይ ናት። የ29 ዓመቷ ሴት የቤቢ ሻወር ግብዣን የጥሪ ካርድ በማህበራዊ ሚዲ ላይ ይፋ ስታደርግ የዜዲ ዊል እና የአምስቱ ሴቶችን ፎቶ ያሳያል።
የግብዣው ወረቀት ላይ ትንሹ ዜዲ ዊልስ ከአንድ እስከ 5 እንኳን ደህና መጣህ የሚል ነበር። ሊዚ ባጋራችው ቪዲዮ ላይ አምስቱ ሴቶች ለሕፃናቱ ጥቅም ሲሉ እርስ በእርሳቸው ለመከባበር እና ለመጠባበቅ ቃል ገብተዋል።በጋራ ባስተላለፉት መልዕክት “ቆንጆ ቤተሰብ እንደሆንን ተመልከቱ፤ ባለቤታችንን እንወዳለን! የልጆቻችንን ህይወት ያማረ ይሆናል መላው ቤተሰቦቻችን ይህንን ተቀብሏል ሲሉ ይፋ አድርገዋል።
ከነፍሰ ጡር ሴቶች መካከል አንዷ የሆነችው ሊዚ ያጋራችእ ቪዲዮ በስፋር ተሰራጭቷል። የተለያዩ አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን ድርጊቱን መፈፀማቻው ሳያንስ በአንድ ዝግጅት ላይ መታደማቸውን “አሳፋሪ” ሲሉ ገልጸውታል። ኒውዮርክ ፖስት ስለ አስገራሚው ቤተሰብ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በሰራው ዘገባ መሰረት ወጣቱ ራፐር የአምስት ልጆች አባት ለመሆን ብስለት እንዳለው ተነግሯል ሲል አስነብቧል።
ከህብረተሰቡ ግፊት ተላቀናል በሚል የሚወሰኑ ውሳኔዎች በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረጉ የፍቅር ግንኙነቶችን እያዳከሙ የቤተሰብን ትክክለኛ መገለጫን እያደበዘዙ መሆኑን በርካቶች አስተያየት ሰንዝረዋል።
በስምኦን ደረጄ

2 Responses