በተጠናቀቀው ግማሽ አመት 19 ሺህ 756 ዜጎችን ከጎዳና ላይ በማንሳት የማቋቋም ስራ መከናወኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ሁሪያ አሊ እንደተናገሩት ባለፉት ስድስት ወራት በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔትና ሥራ ፕሮጀክት 4 ሺህ 550 እንዲሁም ከክልሎችና ከፌዴራል ከተማ አሥተዳደሮች በተገኘ በጀት 15 ሺህ 206 ወገኖችን ከጎዳና ላይ በማንሳት የተቋም አገልግሎት እንዲያገኙ እና ወደ መጡበት አካባቢና ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ተደርጓል።
በጎዳና የሚገኙ ወገኖችን ለማንሣት እንደ ሀገር እስካሁን በተከናወነው ሥራ የተነሺዎች ቁጥር ከነበረበት 39 ሺህ 082 ወደ 54 ሺህ 288 ከፍ ማለቱንም ሚኒስትር ዲኤታዋ መናገራቸውን ብስራት ሰምቷል።
በቅድስት ደጀኔ