ሁቲዎች በቀይ ባህር ወደ እስራኤል የሚሄዱ መርከቦችን ማጥቃት እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ይታወሳል። የቡድኑ ቃል አቀባይ መሐመድ አብዱልሰላም እንደተናገሩት “በቀይ እና በአረብ ባህር ላይ ለአለም አቀፍ የባህር ጉዞ ምንም አይነት ስጋት ስለሌለ ጥቃቱ ይቀጥላል። ኢላማው የእስራኤል መርከቦችን መግታት ነው ሲሉ ገልፀዋል። አብዱልሰላም የዩናይትድ ስቴትስ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጥቃቱ “የመንን ፍልስጤም እና ጋዛን ከመደገፍ ያግዳታክ” ብለው ካሰብ ይሳሳታሉ ሲሉ አክለዋል።
የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ጦር በየመን የሁቲ አማጽያን ላይ ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈፀማቸውን ገልፃዋል። በዋና ከተማዋ ሰነዓ፣ በሁዳይዳህ የቀይ ባህር ወደብ፣ በዳማር እና በሰሜናዊ ምዕራብ የሁቲ ጠንካራ ግዛት ሰአዳ ላይ ድብደባ መፈፀማቸው ተዘግቧል። ፕሬዝዳንት ባይደን ጥቃቱ በኢራን የሚደገፉ ሁቲዎች ከህዳር ወር ጀምሮ በቀይ ባህር መርከቦች ላይ ላደረሱት ጥቃት ምላሽ ነው ብለዋል።
ሁቲዎች አብዛኛውን የመን ግዛት የተቆጣጠሩ ሲሆን ወደ እስራኤል የሚያመሩ መርከቦች ላይ በማነጣጠር ሃማስን እየደገፉ ይገኛል። የሃውቲዎች ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሜሪካ እና እንግሊዝ ለዚህ “ግልጽ ጥቃት” “ከባድ ዋጋ እንደሚከፍሉ” አስጠንቅቀዋል። የሮያል ኤር ሃይል የጦር አውሮፕላኖች በወታደራዊ ተቋማት ላይ “ያነጣጠሩ ጥቃቶችን” ለመፈጸም ረድተዋል ሲሉ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ አክለውም ጥቃቱ “እራስን ለመከላከል የተገደቡ፣ አስፈላጊ እና ተመጣጣኝ እርምጃዎች ናቸው” ብለዋል። ኔዘርላንድስ፣ አውስትራሊያ፣ ካናዳ እና ባህሬን የተልእኮው አካል በመሆን ድጋፍ አድርገዋል ሲሉ ባይደን በበኩላቸው ተናግረዋል።
በስምኦን ደረጄ