በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ማሪያም ቤተክርስቲያን አከባቢ ከተወለደች ሰባት ቀናት የሚሆናት ጨቅላ ህፃን ተጥላ መገኘቱን የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት የአከባቢው ህብረተሰብ አመሻሽ ላይ የህፃን ድምፅ ሰምተው፤ ህፃኗን በህይወት መኖሯን ሲያረጋግጡ ለፖሊስ በማሳወቅ ወደ ህክምና ወስደዋል። የህፃኗ ጤንነት ተረጋግጦ ለቦንጋ ከተማ ሴቶችና ህፃናት የስራ ሂደት ዳይሬክቶሬት እንደተሰጠች ገልፀዋል፡፡
በከተማዉ በተደጋጋሚ ጊዜ ተወልደዉ የሚጣሉ ህፃናት እየተበራከቱ በመምጣቱ ተወልደው የሚጣሉ ህፃናት ማቆያ አለመኖሩ ችግር እንደሆነ ተገልፆል።
ከዚህ ቀደም በከተማ ዉስጥ ተወልደዉ የተጣሉ ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ህፃናት መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን በቦንጋ ገብረፃዲቅ ሆስፒታል ትብብር በማድረግ በጊዜያዊነት እንዲቆዩ ተደርጓል።በጉድፈቻ ለማሳደግ የሚፈልግ ሰዉ ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት በአካል ቀርቦ በሕጋዊ መንገድ መውሰድ ይችላል ተብሏል፡፡
የሰባት ቀን ጨቅላ ህፃን ልጆን ወልዳ የጣለችዉን እናት ፖሊስ እያፈላለገ እንደሚገኝ ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡
በሳምራዊት ስዩም

2 Responses