በቴክሳስ የሞት ፍርድ የተፈረደበት እስረኛ ራሚሮ ጎንዛሌስ እ.ኤ.አ በ2001 በአንዲት ወጣት ግድያ እና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ለአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢልም በስተመጨረሻ በሞት ተቀጥቷል።
ጎንዛሌስ እሮብ እለት መሞቱ ተነግሯል። በሃንትስቪል በሚገኘው የመንግስት ማረሚያ ቤት የኬሚካል መርፌ የሞት ቅጣቱ ተፈፅሞበታል። በወንጀል ድርጊቱ የተገደለችው የ18 ዓመቷ ብሪጅት ታውንሴንድ የተባለች በደቡብ ምዕራብ ቴክሳስ የምትኖረውን ሴት አስክሬኗ በ2001 ከጠፋ ከሁለት ዓመት ገደማ በኋላ የተገኘ ሲሆን ተከሳሹ ተኮሶ መግደሉን አምኗል።በቴክሳስ የወንጀል ፍትህ ዲፓርትመንት በተለቀቀው መግለጫ ጎንዛሌስ ለተጎጂዋ ቤተሰብ ግድያው ከሚፈፀምበት ክፍል በመሆን ደጋግሞ ይቅርታ ጠይቋል።
እኔ በራሴ ላይ ያመጣሁት ህመም፣ የተጎዳሁት ጉዳት ከፍተኛ ነው ከምንም በላይ የነጠቅኩትን ህይወት መመለስ አልችልን የተቀበልኩት ቅጣት በቃላት መግለጽ የማልችለው ነው ብላል። ይህ ይቅርታ በቂ እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ ሲል አክሏል። ይቅር እንድትለኝ መጸለይን አላቆምኩም እናም አንድም ቀን ይቅርታ ለመጠየቅ እድሉን አግኝቼ አላውቅም። ግን አንድ ቀን ይቅር እንደምትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ ሲል ተናግሯል።ሟች ታውንሴንድ በህይወት ብትኖር በዚህ አመት 41 ዓመቷን ትይዝ ነበር።እኤአ በጥር 2001 ከቤቷ ታፍና በጎንዛሌዝ የፆታ ጥቃት ተፈፅሞባት ተገድላለች።
ጎንዛሌዝ ሌላን ሴት በማፈን እና አስገድዶ በመድፈር በእድሜ ልክ እንዲቀጣ ከተፈረደበት በኋላ በታውንሴንድ ግድያ ወንጀለኛ መሆኑ ተደርሶበታል። የሟቿ ታውንሴንድ ወንድም ዴቪድ የጎንዛሌዝን በሞት መቀጣት ከተመለከተ በኋላ በመጨረሻ ፍትህ ሲሰጥ አይተናል ብሏል። ይህ ቀን ለቤተሰባችን ረዥሙ የስቃይ ጉዞ ያበቃበት ቀን ነው ሲል ተደምጧል። ከሁለት አስርት አመታት በላይ፣ ሊታሰብ በማይቻል ስቃይ እና የልብ ህመም አሳልፈናል ሲል ተናግሯል።ዴቪድ የጎንዛሌስ ሞት ትንሽ ሰላም ይሰጠናል ሲል ግን ደስተኛ እንዳልሆንን መናገር እፈልጋለሁ ብሏል።
የጎንዛሌስ ጠበቆች፣ ቦርዱ የሞት ፍርድን ወደ እስር ቅጣት እንዲቀይር ጠይቀው ነበር። እራሱን ለማሻሻል፣ ለማሰላሰል እና ለጸሎት በትጋት ሲደክም ነበር ፤እናም ወደ ጎልማሳ፣ ሰላማዊ፣ ደግ፣ አፍቃሪ እና ጥልቅ ሀይማኖተኛ ተቀይሬ ሲሉ ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥያቄ ቢያቀርቡም ውድቅ ሆኗል።በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ከቴክሳስ እና ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ 11 የሀይማኖት መሪዎች ቡድን የይቅርታ ቦርዱን እና የቴክሳስ ገዥውን ግሬግ አቦትን ግድያው ውድቅ እንዲያደርጉ እና ምህረት እንዲደረግለት ጠይቀዋል።
ሆኖም የምህረት ቦርዱ የጎንዛሌስን የሞት ፍርድ ወደ እስር ለመቀየር 7 ለ 0 ድምፅ በመስጠቱ የሞት ፍርዱ ተግባራዊ ሆናል። የጎንዛሌስ ግድያ በዚህ ዓመት በቴክሳስ ሁለተኛው ሲሆን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ደግሞ ስምንተኛው የሞት ቅጣት ተደርጎ ተመዝግቧል። በተመሳሳይ ሐሙስ እለት ኦክላሆማ እኤእይ በ1984 የ 7 ዓመቷን ህጻን ጠለፋ፣ አስገድዶ መድፈር እና ግድያ የፈፀመው ሪቻርድ ሮጀም በሞት እንዲቀጣ ቀጠሮ ተይዞለታል።
በስምኦን ደረጄ

2 Responses