በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጀሬ ወረዳ ቱሉ ኤጀሬ ቀበሌ ውስጥ ተከሳሽ ታደሰ ሚልኬሳ የተባለ ግለሰብ ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ወንጀሉን ፈፅሟል።
በእለቱ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የ5 ዓመቷን ህፃን ልጅ በተከራየበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት በማስረጃ መረጋገጡን የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት አስታውቋል፡፡
የ5 ዓመቷን ልጅ ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ካደረሰባት በኃላ በከፍተኛ ህመም ስትሰቃይ ቆይታለች። ወላጆቿ የደረሰባትን ሲጠይቋት የተፈፀመባትን ድርጊት በመናገሯ ድርጊቱ ፖሊስ ጆሮ በመድረሱ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን ብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ከኮሙኒኬሽኑ ቢሮ ያገኘው መረጃ ያመላክታል ፡፡
የአስገድዶ መደፈር ጥቃት የደረሰባትም የ5 ዓመቷ ልጅ የህክምና ምርመራ ከተደረገላት በኃላ በተጠርጣሪው ላይ ፖሊስ የወንጀል መዝገብ በማጣራት በሰው እና ህክምን ማስረጃ በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ ልኳል፡፡
አቃቢ ህግም ከፖሊስ የተላከለትን መዝገብ ተመልክቶ ክስ መስርቷል። የቀረበለትን ክስ ሲመለከት የነበረው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ታደሰ ሚልኬሳ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት የምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ኮምኒኬሽን ፅ/ቤት አስታውቋል።
2 Responses