በጋምቤላ ክልል በእናቶችና ህፃናት ጤና ዙሪያ የሚከሰትን ህመምና ሞት ለመከላከል የአፍላ ወጣትነት እርግዝናን መታደግ እንደሚገባ የክልሉ ጤና ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን ያለዕድሜ ጋብቻ፣ የአፍላ ወጣቶች እርግዝና እንዲሁም በኤች አይ ቪ ዙሪያ በጋምቤላ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል ።
በክልሉ ጤና ተቋማት ለእርግዝና ክትትል ከሚሄዱ ነፍሰጡር ሴቶች 26 በመቶ ከ18 አመት እድሜ በታች ናቸው የተባለ ሲሆን ይህም በሴት አፍላ ወጣቶች በሚፈጸም ያለዕድሜ ጋብቻና እርግዝና በእናቶችና ህፃናት ላይ ለሚስተዋለው ህመምና ሞት ከፍተኛ ድርሻ አለው ተብሏል ።
ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያስከትለው የአፍላ ወጣትነት እርግዝና እንዲሁም በኤች አይ ቪ ኤድስ የመያዝ መጠን ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር የሚከሰቱ ችግሮች የመታደግ ጉዳይ የአንድ አካል ሃላፊነት ሳይሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላትና የእያንዳንዱ ሰው የተጠናከረ ተሳትፎን እንደሚጠይቅ ተጠቁሟል ።
ወጣቶችን ከኤች አይቪ ኤድስና ካልታቀደ እርግዝና እንዲሁም ጥንቃቄ ከጎደለው ጽንስ ማቋረጥ እና የአዕምሮ እክል ከሚፈጥሩ ነገሮች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል መባሉን የክልሉ ጤና ቢሮ መረጃ ይጠቁማል ።
በአበረ ስሜነህ

2 Responses