ሆቴሎን ሰርቶ ለማጠናቅ 4 ዓመታት የፈጀ ሲሆን የሆቴሉን ስራ ለማጠናቀቅ በአንድ ወር ውስጥ አንድ መቶ ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጓል። ሀይሌ ሪዞርቶች ግሩፕ ዛሬ በይፍ ስራ የጀመረው ሀይሌ ሆቴል ወላይታ 9ኛ እንደሆነ ተነግራል።
ሀይሌ ሪዞርቶች ግሩፕ ባለቤት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በቀጣይ አንድ አመት 3 ሆቴሎችን የመክፈት እቅድ እንዳለው ያስታወቀ ሲሆን ቦታዎቹም ጅማ ፣ ሻሸመኔ እና ደብረብርሃን ከተሞች መሆናቸውን ገልፃል።
የመጀመሪያ የሀይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች በ2002 ዓ.ም በሀዋሳ የከፈተ ሲሆን በ14 ዓመት ውስጥ መዳረሻውን ዘጠኝ ማድረሱን አስታውቋል።እንደሀገር ያሉትን የሆቴል መዳረሻዎችን እጥረት በከፍተኛ ደረጃ እና ፍጥነት እየቀረፈ መሆኑን የሀይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግረፕ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጋዲሳ ግርማ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
አሁን ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ሀይሌ ሆቴል ወላይታ ሶዶ 107 የመኝታ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን ከ15 እስከ 600 ሰዎችን የሚይዙ የስብሰባ አዳራሾች እንዳላቸውም ተነግሯል።ሀይሌ ሆቴል ወላይታ አገልግሎት ለመስጠት 160 ሰራተኞችን መቅጠሩን የገለፁት አቶ ጋዲሳ ሆቴሉ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ከ300 በላይ ሰራተኞችን እንደሚቀጥር ይጠበቃል።
ሆቴሉ ደረጃውን የጠበቀ የዋና የጅምናዚየም እና የተለያዩ የውበት እና የጤና መጠበቂያ ማአከሎች በስሩ እንዳሉትም የተገለፀ ሲሆን በሆቴሉ ሜኑም የወላይታ ባህላዊ ምግቦች እንደሚካተቱ ተነግሯል።
በቀጣይ በምስራቅ አፍሪካ የመክፈት እቅድ እንዳለው ያስታወቀው ሆቴሉ በአንድ አመት ውስጥ እከፍታቸዋለው ካሉት ሆቴሎች በተጨማሪም ኮንሶ እና ወልቂጤ ላይ የሀይሌ ሆቴል ግንባታ እየተፍጠነ መሆኑ ተገልፃል።
ሀይሌ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ግሩፕ እስካሁን ከ1ሺ800 በላይ ለሚሆኑ ሰዎችን ቋሚ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ የሆቴሎቹ ቁጥር ሲጨምር ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን የስራ እድል እንደሚከፍት አስታውቋል።
በሆቴሉ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል አስተዳደር አቶ ተስፍዬ ይገዙ፤ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ እስካሁን ከገነባው ሆቴሎች አሁን ላይ እየተገነቡ ያሉ ሆቴሎች በግንባታ እቃ እጥረት እና መወደድ ፈተና እየሆነባቸው እንደሆነ የተናገረ ሲሆን አሁንም ግን እየተፈተነም ስራውን በስፍት እንደሚቀጥል አስታውቋል።
በትግስት ላቀው