ብሩክ አበበ ፣ ሙሉጌታ ሀይሉ እና መኳንንት የኔዓለም የተባሉ ሦስት ወንጀል ፈፃሚዎች ጥር 17 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት 12 ሠዓት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ካራቆሬ መድሃኒያለም ቤተ ክርስቲያን ጀርባ አካባቢ የግል ተበዳይ አቶ ተስፋዬ ግርማን በማስፋራራት እና ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት በማድርስ ግምቱ 27 ሺ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ሞባይል ስልክና 4ሺብር ቀምተው ለማምለጥ ሲሞክሩ በስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ የክትትል አባላት አማካኝነት ብሩክ አበበ የተባለው እጅ ከፍንጅ መያዝ ተችሏል፡፡
ከወንጀል ፈፃሚው እጅ የግል ተበዳይ ስልክና መንጃ ፈቃድ መገኘቱን በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ የካራ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ም/ኢ/ር ተመኙ ያለ ገልፀዋል፡፡ሙሉጌታ ሀይሌ እና መኳንንት የኔዓለም የተባሉት ወንጀል ፈፃሚዎች ወደ ገደል ዘለው በመግባት ያመለጡ ቢሆንም ሲዘሉ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ ህክምና ለማግኘት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ፖሊስ በደረሰው መረጃ መሰረት ወንጀል ፈፃሚዎቹ አለርት ሆስፒታል ሲታከሙ በቁጥጥር ውለዋል። ከግለሰቡ ላይ የተሰረቀው 4ሺ ብር በኤግዚቢትነት መያዙን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ፖሊስ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ወንጀሉን በፈፀሙ በሰዓት እድሜ ውስጥ በቁጥጥር አውሎ እና ንብረታቸው በማስመለሱ የተሰማቸውን ደስታ የገለፁት አቶ ተስፋዬ ግርማ ፖሊስ በሥውር የሚያደርገው ጥበቃ ለዚህ ውጤት እንዳበቃው መገንዘባቸውን ጠቁመው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ፖሊስ ጣቢው ባከናወነው ምርመራ የማስፋት ስራ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ/ም ወረዳ 2 ልዩ ስፍራው ቻይና የድንጋይ ጠጠር መፍጫ አካባቢ እና ጥር 12 ቀን 2016 ዓ/ም በተመሳሰይ ስፍራ ወንጀል ፈፃሚዎቹ ከሁለት ግለሰቦች የቀሙትን ሁለት ስልኮች አስመልሷል።
ፖሊስ ግለሰቦቹ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርመራውን አጠናቆ መዝገቡን ለአቃቢ ህግ መላኩን ከኃላፊው ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡

2 Responses