ከታገዱት ውስጥ 44 ዓይነት የምግብ ዘይት እና 39 ዓይነት የምግብ ጨው ምርቶች ደህንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡ በመሆናቸው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ይፋ ሆነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው እና የምግብ ዘይት ላይ በተደረገ የገበያ የቅኝት ስራ የገላጭ ጽሁፍና የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ሳያሟሉ እንዲሁም ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ ገበያ ላይ የዋሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡
የባለስልጣኑ የህዝብ እና ኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ አበራ ደመቀ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቭዥን እነደተናገሩት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰራው የገበያ ቅኝት ስራዎች እንዳረጋገጠው 44 ዓይነት የምግብ ዘይት ምርት እና 39 ዓይነት አዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው ምርት ደህንነታቸውና ጥራታቸው ያልተረጋገጡ እንዲሁም የሀገሪቱን አስገዳጅ ደረጃ እና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ መገኘታቸው ገልጸዋል፡፡
በገበያ ላይ የዋሉት ምርቶችን የገበያ ቅኝት ስራዎችን በማጠናከር እና የቁጥጥር መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ እራሱ የቁጥጥር ባለቤት እንዲሆን ሲያደርግ መቆየቱ ዳሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም በየደረጃው ከሚካሄዱ በርካታ የቁጥጥሩ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የገበያ ቅኝት ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ ምግቦች ላይ ባደረገው የገበያ ቅኝት በአዮዲን የበለፀገ የምግብ ጨው እንዲሁም ለምግብነት የሚውሉ የተለያ ዓይነት ማለትም የበቆሎ፣ የሰሊጥ ፣ የኦቾሎኒ ፣ የሱፍ አበባ ፣ የጥጥ ዘይት እና የአትክልት ዘይት የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃ ያላሟሉ እና የደረጃ ምልክት ያለጠፉ ምርቶችን መለየታቸውን አቶ አበራ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
በምርቱ ላይ ስለምርቱ የተለጠፉ ወይም የተፃፉ የምርት ገላጭ ፅሁፍ የኢትዮጵያ እስታንዳርድ ኢንስቲቲዩት ያወጣው አስገዳጅ ደረጃ CES 73 2013 ያላሟሉ ሲሆን በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች የአምራች ድርጅት ስም ያልተጠቀሰ፣ የአምራች አድራሻ ያልተገለፀ፣ የኢትዮጵያ አስገዳጅ የደረጃ ምልክት የሌለው፣የምርቱ መለያ ቁጥር የሌለው፣የምርቱ ጥሬ ግብዓት ዝርዝር ያልተገለፀ፣ የመጠቀሚያ እና የማብቂያ ጊዜ የሌላቸው ምርቶች መሆናቸው ተለይተዋል፡፡ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተከለከሉት የዘይትም ሆነ የጨው ምርቶች ዝርዝር ተያይዛል፡፡
አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያማሉ ገበያ ላይ የተገኙ
የምግብ ዘይት ምርቶች ዝርዝር
1. ሰመር ንፁህ የምግብ ዘይት
2. ማሚ የተጣራንፁህ የምግብ ዘይት
3. እስካይ /Sky Sun flower oil
4. ሳኒ /SANI Edible Cooking Oil)
5. አዚማር/Azimar Sunflower Oil
6. ኑራ ንፁህ የምግብ ዘይት
7. አበባ ንፁህ የምግብ ዘይት
8. አደይ ንፁህ የምግብ ዘይት
9. ዘቢብ/Zebib Sunflower oil
10. አስሊ ንፁህ የምግብ ዘይት
11. ሪል (Real Pure Food Oil)
12. ዙፋን ንፁህ የምግብ ዘይት
13. ሀኒ(Hani Sunflower Oil)
14. ዲና ንፁህ የምግብ ዘይት
15. ሊና ንፁህ የምግብ ዘይት
16. ማማ የተጣራ የምግብ ዘይት
17. አል ኑር Al-Nur Sunflowor Oil
18. ዋሪዳ Warida sunflower Oil
19. ዜድ ንፁህ የምግብ ዘይት
20. ደሴት ንፁህ የምግብ ዘይት
21. ከፍታ ንፁህ የምግብ ዘይት Pure Food Oil
22. ንግስት ንፁህ የምግብ ዘይት Nigist pure Food oil
23. ሸገር Sheger pure Edible Oil
24. አሪፍ Arif የኑግ የምግብ ዘይት
25. አመለ AMEL Edible Oil
26. ብሉ የኑግ ዘይት
27. ንፁህ Nitsuh Food Oil
28. ኡማ ንፁህ የምግብ ዘይት
29. ማዕድ Maed ንፁህ የምግብ ዘይት
30. ሀያት የተጣራ የምግብ ዘይት
31. የምስራች ንፁህ የምግብ ዘይት
32. ህብረት ንፁህ የምግብ ዘይት
33. ጎንደር የምግብ ዘይት Gonder Food Oil
34. ዜማ Zema pure Edible Oil
35. ፋና fana
36. ናና የኑግና የለውዝ የምግብ ዘይት
37. ሪም ንፁህ የምግብ ዘይት
38. አንድነት ANDNET
39. ሲያም ንፁህ የምግብ ዘይት
40. ቤላ የምግብ ዘይት
41. ሐሊማ የምግብ ዘይት
42. ወሲላ ንፁህ የምግብ ዘይት Wesila
43. ዝና ንጹህ የምግብ ዘይት
44. ሰነዓ ንጹህ የምግብ ዘይት
#ተጨማሪ
አስገዳጅ የሀገሪቱን ደረጃና የገላጭ ጽሁፍ ደረጃን ሳያማሉ ገበያ ላይ የተገኙ
የምግብ ጨው
1. አርኪ የገበታ ጨው ARKY IODIZED SALT
2. ኢኮ አዮዳይዝድ ጨው EKKO IODIZED SALT
3. ስጦታ ጨው SITOTA Iodized Salt
4. መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFIND & IODIZED SALT
5. አስቤዛ የገበታ ጨው Asbeza Iodized salt
6. ዘሀራ የገበታ ጨው ZAHARA IODIZED SALT
7. መነስ ጨው MENES IODIZED SALT
8. ግዩን አዮዲን ጨው Ghion Iodin Salt
9. አርዲ የገበታ ጨው ARDI IODIZED SALT
10. ሳሊህ የገበታ ጨው SLIHA IODIZED SALT
11. ናና ጨው NANA SALT
12. ቤስት የገበታ ጨው Best Iodized Salt
13. ቅመም የገበታ ጨው Iodized Salt
14. ረሃ የገበታ ጨው REHA IODIZED SALT
15. አርዲ የገበታ ጨው ARDY IODIZED SALT
16. አፊአ የገበታ ጨው AFIA IODIZED SALT
17. ፋና የገበታ ጨው Fana table salt
18. እቴቴ የገበታ ጨው Etete Iodized Table Salt
19. ልዩ ጣዕም የገበታ ጨው LIYU TAEM IODIZED Salt
20. ሀሮኒ HARONI Table Salt
21. ሮም ROME ንጹሁ የገበታ ጨው
22. ቶፕ የገበታ ጨው TOP IODIZED SALT
23. ጤና ጨው Tena Iodized salt
24. ማሬ የገበታ ጨው MARE IODIZED SALT
25. ሳፊ የገበታ ጨው SAFI IODIZED SALT
26. እሜቴ አዮዳይዝድ የገበታ ጨው Iodized Table Salt
27. ሀላል የገበታ ጨው HALAL IODIZED SALT
28. ጡልት ጨው TULIT SALT
29. ሪል የገበታ ጨው REAL IODIZED SALT
30. ጎልድ GOLD IODIZED SALT
31. ስፔሻል የገበታ ጨው SPECIAL Iodized Table Salt
32. ሰላም የገበታ ጨው IODIZED SALT
33. ሸሙ በአዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው SHEMU IODIZED SALT
34. ኢምሬት ጨው Emirate salt
35. ኑር NUR IODIZED SALT
36. ሀገሬ አዮዳይዝድ ጨው HAGERE Iodized Salt
37. ኢቲ ኤምኢየገበታ ጨው ET ME IODIZED SALT
38. ማራኪ MARAKI በአዮዲን የበለጸገ የገበታ ጨው
39. ታሪክ የገበታ ጨው TARIK TABLE SALT
በትግስት ላቀዉ